ቴሌብር የኢትዮጵያ ቀዳሚ ሱፐር አፕ እና የቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ስፖንሰር ተጠቃሚዎችን ያለምንም እንከን የለሽ የግብይት አቅም እያጎናጸፈ ይገኛል። ቴሌብር ትኬቶችን በኦንላይን ላይ ከመግዛት ጀምሮ በኤክስፖው ላይ ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን ለተጠቃሚዎች ሽያጭ ያለምንም ኮሚሽን ብር መሰብሰቢያ ፕላትፎርም ሆኖ በምቾቶት የዲጂታል ፈጠራን እያበረታታ ይገኛል።
ቴሌብር በአሁን ግዜ የኢትዮጵያ የሱፐር አፕሊኬሽን አጠቃቀማችንን ከዲጂታል እና ፋይናንሺያል አገልግሎቶች ጋር በአንድላይ እየተለወጠ ይገኛል። የቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ርዕስ ስፖንሰር እንደመሆኑ መጠን ለሚሊዮኖች ምቹ እና ተደራሽነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ቦታ ይይዛል። ዕቃዎችን እየገዙ፣ ሂሳቦትን እየከፈሉ ወይም ለልዩ ልዩ ዝግጅቶች ትኬቶችን ሲገዙ፣ ቴሌብር ፍላጎቶን ሁሉ ወደ አንድ መተግበሪያ ስለሚያመጣላችሁ ቀላል ያደርግሎታል።
ለኤክስፖ ፕሮግራሞች ልምድ ጨዋታ ቀያሪ መተግበሪያ
በቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤግዚቢሽን ቴሌብር የትኬት መግዣ እና የኤግዚቢሽን ሽያጭ ተመራጭ ሆኖ ደምቋል። የመተግበሪያው የነጋዴዎች መገበያያ ክፍል አቅራቢዎች ምርቶችን በቀጥታ ለደንበኞች እንዲሸጡ ያስችላቸዋል፣ ይህም ለተጠቃሚዎች እንከን የለሽ የግዢ ልምድ ይፈጥራል። ጎብኚዎች ያለ ምንም ችግር እና መንገላታት በእጅ ስልካቸው በጥቂት ገጽ ሽግግሮች ብቻ መክፈል እና መግዛት ይችላሉ።
የኤክስፖው ልዩ ክስተት የሆነው ቴሌብር መተግበሪያ ተጠቃሚዎች የጥሬ ገንዘብ ለማግኘት የሚደረገውን እና የወረፋ ሰልፍ እንግልት በማስቀረት ኤክስፖ ቲኬቶችን በኦንላይን እንዲገዙ ያስችላቸዋል። ለተጠቃሚ ምቹ በሆነ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መተግበሪያ የክፍያ አማራጮች መጠቀም እንደዚህ ዘመን ቀላል ሆኖ አያውቅም። ቴሌብር ከኤክስፖ አስተዋጾ ባሻገር የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የማዕዘን ድንጋይ ነው። ገንዘብ-አልባ ክፍያዎችን፣ የሞባይል ዋሌት አገልግሎቶችን እና የነጋዴ ግብይቶችን በማስጀመር በከተማ እና በገጠር ማህበረሰቦች ውስጥ የፋይናንስ ማካተት እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማሳደግ ላይ ይገኛል።
ቴሌብርን ምን ልዩ ያደርገዋል?
- ሁለገብ መተግበሪያ (Super App)፡ ከመገልገያ ክፍያ፤ ትኬት መግዢያ፤ እና ጽሑፍ መላላኪያ ድረስ ቴሌብር ሁሉንም ይሸፍናል።
- የግብይት ክፍያዎች፡ የሱቅ፣ ቢል እና የጉብኝትዎን በኦንላይን ላይ ሽያጮችን ቀለል ያደርጋል።
- ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ፡ በጠንካራ ደህንነት እና እንከን የለሽ ግብይቶች ማድረግ መቻሉ።
- አካታች መዳረሻ፡ በስማርት ስልኮች እና በመደበኛ የሞባይል መሳሪያዎች በUSSD አገልግሎቶች ተደራሽ መሆኑ።
የመተግበሪያውን ሙሉ አቅም ለማወቅ በቴሌብር አዲስ ገና 2017 ኤክስፖ ላይ የቴሌብር ድንኳኖችን እና ማሳያ ቦታዎችን ይጎብኙ። ስለ አዳዲስ ፊቸሮች ይወቁ እና ቴሌብር በኢትዮጵያ የወደፊት የዲጂታል ክፍያዎችን እንዴት እየገራ እንዳለ በተግባይ ይጎብኙ።


